ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሴራሊዮን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ሀበሻ ለፍቅር በሚል ማህበር የታቀፉት የኮሚኒቲ አባለቱ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲያስፖራውን ተሳትፎ፣ በኢትየጵያ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ እና በሌሎች ጉዳዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ባለው ለውጥ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የኮሚነቲ አባለቱ ለውጡ በመካከለኛውና በታችኛው እርከንም ሊተገበር ይገባል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከለከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ሊተገበር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

"በያዝናቸው የለውጥ መንገዶች የለውጡ አንዱ ትልቅ ደጋፊና አጋር ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ያለው በውጪ የሚኖረው ማህበረሰብ ነው" ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የለውጡ ጉዞ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ (ምንጭ፡-ኢቲቪ)