ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ ።
ውይይቱም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተገልጿል ።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሴሪል ራምፓሳ በዘንድሮ ዓመት ህዳር ወር ላይ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል ።
በዛሬው ዕለት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖከ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ያደረጉት ውይይት ከፕሬዚዳንት ሴሪል ጋር የተደረገው ውይይት ቀጣይ ክፍል በመሆኑ ተገልጿል ።