በአገሪቱ እየተስተዋለ ያለው የመሠረተ ልማት ግንባታዎች መጓተት ችግር ተቀናጅቶ ባለመሥራት የሚፈጠር ነው ተባለ

በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ ትላልቅ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች መጓትት ተቀናጅቶ ባለመሥራት ምክንያት የሚፈጠር  ችግር ነው ተባለ ።    

በሴክተሩ ላይ የሚስተዋለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የማስተር ፕላን ዝግጅት ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የፌዴራል የተቀናጀ የመሠረተ ልማቶች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ከባለድርሻ አካላት ዳር በቢሾፍቱ ከተማ ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ አስታውቋል ፡፡

የፌዴራል የተቀናጀ የመሠረተ ልማቶች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አልማው መንግስቴ በመድረኩ እንደገለጹት በአገሪቱ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ወቅት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በቅንጅት ባለመሥራታቸው ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የሀገር ሀብት ብክነት ፤ ለግንባታዎች ጥራት መጓደል እና መጓተት  ዋነኛው ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

ከካሳ ጋር ተያይዞ ያለው የህብረተሰቡ የግንዛቤ ደረጃም ለማሳደግ  በሥራቸው ላይ ትልቅ ጫን እንዳለውም አክለዋል ፡፡ 

በስፋት በሴክተር መስሪያቤቶቹ ላይ የሚስተዋለውን በቅንጅት ያለማቀድ እና ያለመተግበር ችግርን ለመፍታት ያስችል ዘንድም የማስተር ፕላን ዝግጅት ማዕቀፍ መዘጋጀቱን በቀጣይ ሥራቸውን በተሻለ መግባባት ለመስራት አጋዥ መሆኑም በውይይት መድረኩ ተነስቷል ፡፡