ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን ገበኙ

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት  ጎብኝተዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በጉብኝታቸው ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በትምህርት ቤቱ ሁኔታ  ውይይት አደርገዋል።

በቆይታቸውም በትምህርት የተለያዩ   ችግሮች ዙሪያ እና በመፍትሄዎቻቸው ላይ ውይይት  አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል (ዶርሚተሪ) እጥረት እንዳለ የተገለፀ ሲሆን፥ በተለይም ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከዶርሚተሪ ውጭ ለመኖር መገደዳቸው ተጠቅሷል።