በሶማሊያ ደቡባዊ ግዛት በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አልሻባብ መወዳደር እንደማይችል ተገለጸ

በሶማሊያ እንደሁለተኛ አስተዳደር የሚቆጠረው  የወታደሮች ቡድን አልሸባብ በሀገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ላይ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ መወዳደር እንደማይችሉ የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል በተሰጠው መግለጫ የአልሸባብ ምክትል መሪ  ሙክታር ሮቦው   አሁን ባለው ሁኔታ ለፖለቲካ  አመራርነት  ለመወዳደር  ብቁ አይደሉም ብለዋል፡፡

አለም አቀፍ የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ከመጠበቅ አንፃር ሮቦው  አሁንም በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት የተቀመጠባቸው እገዳ እንዳለ ነው፡፡

በመሆኑም ሰውዬው  በደቡብ ምዕራባዊ ክልላዊ መንግስት  በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ መወዳዳር አይችሉም ተብሏል፡፡  

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም ሮቦው  ወደ ፕሬዚዳንቱ  ቢሮ ለመግባት የሚደረገው ወድድር ላይ ለመካፈል  የተቀመጡ  ቅድመ ሁኔታዎችን  አያሟሉም   ብለዋል፡፡

አቡ መንሱር በመባል የሚታወቁት ሮቦው ባሳለፍነው ሀሙስ በባዳኦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊት ቆመው ለፕሬዚዳንታዊው ምርጫ እጩ  መሆናቸውን  አስታውቀው ነበር ፡፡

በሱማሊያ ከሚገኘው  የቪኦኤ  ድምፅ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉት ሮቦው የሀገሪቱ መንግስት በሳቸው ላይ የሰጠውን  መግለጫ አስመልክቶ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

ሮቦው  በአፍጋኒስታን ከአልቃኢዳ የሽብር ቡድን  ስልጠና  ወስደው በአንድ ወቅትም  በአል-ሸባብ ውስጥ ከፍተኛ ወታደራዊ  አዛዥ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2012 የኦባማ አስተዳደር በጠቅላላው ሮቦውን ጨምሮ የሽብር ቡድኑ አባሎች ቦታ ላይ መረጃ ለማግኘት እስከ 33 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማፍሰሳቸውም ይታወሳል ፡፡

ነገር ግን በዚያው ዓመት ሮቦው የቡድኑ ኢሚር – አህመድ ጎኔኔን በ2014 በአሜሪካን አውሮፕላን ማረፊያው በመገደላቸው በግል ጠባቂዎቻቸው ተከበው  ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡/ቪ ኦ ኤ/