በኡጋንዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ከ40 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ400 በላይ ጠፍተዋል

በኡጋንዳ  በኤልጎን ተራራ አቅራቢያ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት በአከባቢው የሚኖሩ  ከ 40 በላይ ሰዎች ህይታቸውን ሲያጡ ከ 400 በላይ የሆኑት ደግሞ ጠፍተዋል ፡፡

በምሥራቃዊ የኡጋንዳ ክፍል ጥሎት የነበረውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተፈጠረው የመሬት መንሸራተት በአከባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እስካሁንም ከ40 በላይ ሰዎች በአደጋው ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

የመንግሥት ህይወት አድን ቡድኖች ወደ ወደ ስፍረው ደርሰው  እገዛ ሲደርጉ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ስጋት አለ ተብሏል ፡፡

በአከባቢው የጣለውን  ኃይለኛ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተው ጉርፍ ሳቢያ የተፈጠረው የመሬት  መንሸራተት የቡዳዳ መንደርን ጠራርጎ ውስዶታል ነው የተባለው ፡፡ ሰዎችም በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ለማትርፍ ሲረባረቡ ነበር ፡፡

በኡጋንዳ የአደጋ መከላከል ኃላፊ የሆኑት ማርቲን ኦዎር ሱሜ ወንዝ በመሙላት ድንበሩን ጥሶ ወደ ቡዱዳ መንደር ኃይለኛ ጎርፍ በመፍጠሩ በአከባቢው በቡዳዳ  ወረዳው  ላይ  የመሬት መንሸራት በመከሰቱ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ እ.ኤ.አ በ 2010 በቡዱዳ ተከስቶ የነበረው የመሬት መንሸራትት ከ 300 መቶ በላይ ለሆኑ ሰዎች ህልፈት ምክንያት መሆኑም ይታወሳል ፡፡

አከባቢው በእሳተ ጎሞራዎች የተሞላ ተራራማ ስፍራ እና ለግብርና ምቹ ከመሆኑ ጋር ተያይዙ ከፍተኛ የሆኑ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሰፍረውበታል ይህም በአከባቢው ላይ ተፅእኖን ፈጥሩዋል ያሉት በካማፓላ የቢቢሲ ሪፖርተር  የሆኑት ፓተንስ አውተሪ ናቸው ፡፡

በዚህ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከዚህ ቀደም ከደረሰው አደጋ በኋላ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ቢደረግም አብዛኞቹ ግን ወደ አከባቢው ተመልሰው መጥተዋል ፡፡

የኡጋንዳ ቀይ መስቀል ቡድን እስካሁን የ36 ሰዎች አስክሬን ማግኘታቸውን ሲናገሩ ነገር ግን የአካባቢው ባለሥልጣን በእለታዊው ጋዜጣቸው ላይ እስካሁን ድረስ 40 የሚሆኑ አስክሬኖች  ማግኘታቸውን ነው የገለፁት ፡፡

የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ጉዳት የደረሰበት ቦታ ላይ ድጋፍ የሚያደርጉ እና የጠፉ ሰዎችን የሚፈልግ አደን ቡድን አርብ ዕለት ወደ ሥፍራው ልኳል ፡፡

የሱሜ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ጆናታን ሙሴኒ የመሬት መንሸራተቱ ከ 1 ሺ 5 መቶ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን ወደ አከባቢው ለመግባት የሚያስችሉ መንገዶችም  በአደጋው መፈራረሳቸውን ተናግረው  በመሬት መንሸራተቱ  ከ 200 በላይ የሆኑ የሺቲቲያ  የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  የተወሰዱ መሆናቸውም አክለዋል ፡፡

በኡጋንዳ የአደጋ መከላከል ኃላፊ የሆኑት ማርቲን ኦዎር  ሱሜ ወንዝ በመሙላት ድንበሩን ጥሶ ወደ ቡዱዳ መንደር ኃይለኛ ጎርፍ በመፍጠሩ በአደባቢው በቡዳዳ  ወረዳው  ላይ   የሜሬት መንሸራት በመከሰቱ ከፍተኛ ጉዳት አድረሱዋል ፡፡

ኦዎር እንደገለጹት በብሪግ ስቲቨን ኦሉካ የሚመራው የኡጋንዳ  አደጋ መከላከል  እና የመልሶ ማቋቋም  ቡድን ወደ ስፍረው በማቅናት  የድንገተኛ አደጋ የሚያስፈልጉ  ቁሳቁሶችን ፤ ድንኳኖችን፤ የብርድ ልብሶች፤ የውሃ መያዣ እን ምግቦችንም በስፍረው በማከፋፈል   ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል ፡፡ (ምንጭ:ከቢቢሲ እና ከቦብሰርቨር)