337 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – 3መቶ 37 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደረሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ  አቀባባል እንዳደረጉላቸው ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።