34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

                                     34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ እንደሚጀመር ተገለጸ።

ጉባኤው “በኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ቅርስ የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፣ የህብረቱ መሪዎች በተለያዩ አህጉራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ባመጣው የማህበረ ምጣኔ ሀብት ጫናን እንዴት ማገገም እንዳለባትም ሀሳብ ቀርቦ ሊወያዩበት እንደሚችሉ እየተጠበቀ ነው።

ዘንድሮ በይፋ ወደ ተግባር የገባው አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ወቅታዊ አፈጻፀም ላይም ውይይት እንደሚደረግ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።