354 ዜጎች ከሊባኖስ ተመለሱ

የካቲት 25/2013 (ዋልታ) – 354 ኢትዮጵያዊያን ኤልማ የተባለ ድርጅት ከፍሪደም ፈንድ እና የኢ.ፌዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ከሊባኖስ ቤይሩት ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።