4ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

                 4ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ ለመከላከያ ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ 4ኛው የማስ ስፖርት ላይ ተሳትፈዋል።

ምክትል ከንቲባዋ በመዲናዋ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የስፖርት የማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በተካሄደው 4ኛዉ ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የከተማ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡