የኢትዮጵያ ኢቨስትመንት ፎረም በዶሃ ተካሄደ

"በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ" በሚል መሪ ቃል የአገሪቱን የኢንቨስትመንት ምቹነት ለማስተዋወቅ ያለመ ፎረም በኳታር ዶሃ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል።

በፎረሙ ከ25 በላይ የኳታር ንግድ ምክር ቤት እና የኩባንያ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በኳታር የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ ማብራሪያና ገለጻ ተሰጥቷል።

በዚሁ ፎረሙ የተሳተፉት ባለሀብቶችና የካምፓኒ ተወካዮች በተሰጠው ገለጻና ማብራሪያ ጠቃሚ መረጃ ማግኘታቸውን ገልጸው በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)