የጤናማ እናትናት ወርን ምክንያት በማድረግ የጤና ሚኒስቴር የደም ልገሳ ፕሮግራም ሊያከናውን መሆኑ ተገለጸ ።
የጤናማ እናትነት ወርን ምክንያት በማድረግ በመጪው ሰኞ እና ማክሰኞ (13-14/2011ዓ.ም) ለጤና ሚኒስቴር ሠራተኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም እየተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሣ ገልፀዋል ።
ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶችም ተመሳሳይ ፕሮግራም በማዘጋጀት ሠራተኞቻቸው እናቶችን ለመታደግ ደም መለገስ እንዲችሉ እንዲደረግ ዶ/ር ተገኔ ጥሪ አቅርበል ።(ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር)