ጃፓን በ 2030 ጨረቃ ላይ የጠፈር ተመራማሪዎቿን ለመላክ ማቀዷን ይፋ አደረገች

ጃፓን በ2030 ጨረቃ ላይ የጠፈር ተመራማሪዎቿን ለመላክ ማቀዷን ይፋ አደረገች ።

የጃፓን መንግሥት  ቃለአቀባይ ለሲ ኤን ኤን በሰጡት መግለጫ ጃፓን   ጨረቃ ላይ  ተመራማሪዎችን መላክ ያስፈለጋት  ዋነኛ ምክንያት የጨረቃን ገጽታ ለመመርመር መሆኑን ገልፆ  ጃፓን ወደ ህዋ የምታደርገዉ ጉዞ  የአለምአቀፍ ተልእኮ  አካል እንደሆነ ገልፃለች፡፡

ጃፓናውያኑ ይህ እቅዳቸው ከተሳካላቸው ለጃፓን ኤሮስፔስ ኤክስፕሎሬሽን ኤጄንሲ ጃቫ የሰው ልጅ ወደ ጠፈር በመላክ የመጀመሪያ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ቃለአቀባዩ  ለ ሲ ኤን ኤን እንደገለፁት  ጃፓን በቀጣይ የምታደርጋቸውን የህዋ ሳይንስ የምርምር እቅዶች እኤአ በ መጋቢት 2018 ጃፓን በምታዘጋጀው  አለምአቀፉ የህዋ ሳይንስ ግኝቶች ፎረም ይፋ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡

ሃገሪቱ በቴክኖሎጂ ልህቀት የምታደርገው አስተዋፅኦ በህዋ ሳይንሱ በመሪነት  ከሚጠቀሱት  ሀገራት ጋር ጃፓንንም በቅድሚያ ሊያሰልፋት እንደሚችል እና የጃፓን  ፍላጎት ግን ጃፓን ጨረቃ ላይ ሮኬቶችን ለማምጠቅ ሳይሆን በአለምአቀፉ የህዋ ሳይንስ ምርምር የራሷን አስተዋፅኦ ለማበርከት እንደሆነ ነው የተገለፀው ፡፡

የጃቫ ቃለአቀባይ እንደተናገው የጃፓን የህዋ ሳይንስ ምርምር ግኝቶች ጃፓን እኤአ  በመጋቢት 2018  በምታካሄደው  ኢንተርናሽናል የህዋ ግኝቶች ፎረም ይፋ እንደምታደርግ አስታዉቃለች፡፡

 
ጃፓን የእስያ ሀገራት አሜሪካና ሩስያና እና ቻይና ቀጥላ አለምአቀፉን የህዋ ሳይንስ ምርምር ላይ  የላቀ ውጤት ግስጋሴዋን ቀጥላለች፡፡

 

በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በቀዝቃዛው  ጦርነት ወቅት በአሜሪካ ሩስያ ህንድ እና ቻይና   ስትራቴጂዎች መካከል የተካሄደውን የጠፈር ምርምርላይ በሚደረግ  ውድድር  የበላይነት ሲያሳዩ ቆይተዋል፡፡

አሁን ደግሞ ጃፓን የህዋ ሳይንስ ምርምር ላይ በምታደርገዉ ግስጋሴ አጠናክራ ለመቀጠል ምርምሯን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ቻይናም ሌላኛዋ የእስያ ሀገር የጠፈር ተመራማሪዎቿን ወደ ህዋ ለመላክ  ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ የምትገኘው  ቻይና ጠፈርተኞችን ወደ ህዋ ለመላክ የምታደርገው ጉዞ  ረጅም ግዜ አይፈጅባም ሲሉ አንድ የቻይና የህዋ ሳይንስ የከፍተኛ ባለሥልጣን  ለሀገሪቱ  መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡

ጃፓን በበኩሏ  ወደ ህዋ ሳይንስ የምታደርገውን ምርምር አጠናክራ በመቀጠል በህዋ ሳይንሱ የላቀ አስተዋፅኦ ለማድረግ ክንዷን አፈርጥማች፡፡  እንደ ጃፓን የቀጣይ እቅዷን ከተሳካላት በ2025 በጨረቃ ኡደት ላይ አዲስ የየህዋ ጣቢያ ለማቋቋም ትልቅ ተስፋ አላት፡፡