5ኛው ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ተዋጊ መሃንዲሶችን አስመረቀ

 

በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ያሰለጠናቸውን የተዋጊ መሃንዲስ ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡

በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የተሰጠው ስልጠና የተቀነባበሩ ፈንጅዎችን ማስወገድ ፣ በኮንቦይ እጀባ ወቅት የመንገድ ፍተሻ ማድረግ እና የተቀበረ ፈንጅን ማስወገድ በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

የኡንማስ አገናኝ ኬቬን ኪዘላ እንደተናገሩት ስልጠናው በተሰማሩበት ግዳጅ ክህሎትና አቅም አግኝተው የሰራዊቱ ደህንነት እንዲጠበቅ ስልጠናው አጋዥ ነው ፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮነን በበኩላቸው ከግዳጅ ቀጠናው አንፃር የተሰጠው ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል አያይዘዉም ቀጣይ ለሚወጣው ግዳጆች የተመራቂዎች ሚና የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የሻለቃው ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ስንታየሁ ለታ ያልፈንዱ መሳሪያዎች ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት የማስወገድ ትምህርት መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

የተሰጠው ስልጠናውመ ሞያተኞቹ የነበራቸውን አቅምና ችሎታ የበለጠ ያጎለበቱበት ነው ብለዋል፡፡

የሻለቃው መሃንዲስ ሃላፊ ሻምበል እንግዳወርቅ ጌታነህ የተሰጠው ስልጠና የአልሸባብን እንቅስቃሴ ማዕከል ያደረገና ለሞያተኞቹ ትልቅ አቅም የፈጠረ  ነው ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡