6ኛው ሳምንት የፅዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ተካሄደ

ሚያዚያ 02/ 2013 (ዋልታ) – አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና ፅዱ ከተማ ለማድረግ “አካባቢዬን በማፅዳት ለከተማዬ ውበት አምባሳደር ነኝ” በሚል ለ6ኛ ሳምንት የአካባቢ ፅዳት ዘመቻ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤት ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ከተማዋን ፅዱ የማድረግ የዘመቻ ብቻ ሳይሆን የእለት ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በጽዳት ዘመቻው የክፍለ ከተማ እና የወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች፣  አርቲስቶች፣  የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የጸጥታ አካላት፣ የጽዳት ሰራተኞች እንዲሁም ነዋሪዎች እና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

(በትዕግስት ዘላለም)