6ኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 እንዲካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተቆረጠለት

6ኛው አገራዊ ምርጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን 6ኛ አገራዊ የምርጫ ለማካሄድ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

የድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው የተቀመጠ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን በረቂቁ ተመላክቷል።

ግንቦት 28 እና 29 ቀን 2013 ዓ.ም ለአገር አቀፍ ምርጫ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ውጤት የሚገለጽባቸው ቀናት እንዲሆኑም በረቂቁ ተቀምጧል።

ከግንቦት 29 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ የምርጫ ውጤት የሚገለጽበት ጊዜ እንደሚሆንም የቦርዱ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አመልክቷል።

የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ከየካቲት 08 ቀን እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሆን ተቀምጧል።

የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድበት ከየካቲት 22 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ በጊዜያዊነት ቀን ተቆርጦለታል።

ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው የትግራይ ክልልን እንደማይመለከትም ተገልጿል።