7.6 ሚሊየን ዜጎች የሚሳተፉበት 2ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ

መስከረም 10/2014 (ዋልታ) – በተራዘመው ሁለተኛው ሀገራዊ ምርጫ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዜጎች እንደሚሳተፍበት ተገለጸ፡፡
ቦርዱ የዝግጅት ሂደቱን በተመለከተ ያለውን ሂደት ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

መስከረም 20 ለሚከናወነው ምርጫ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም 30 ሺህ የሚጠጉ የምርጫ አስፈጻሚዎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በደቡብ፣ ሱማሌ እና ሀረሪ ክልሎች መስከረም 20 በሚደረገው ምርጫ 47 ለክልል ም/ቤት 105 ደግሞ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተዘጋጁ ምርጫ ክልሎች መኖራቸውንም አማካሪዋ ተናግረዋል፡፡

22 የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ 1ሺህ 236 እጩዎች በምርጫው መቅረባቸው ተገልጿል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔውም በተያዘለት ቀን መስከረም 20 አብሮ የሚከናወን መሆኑም በመግለጫው መጥቀሳቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!