ዋልታ ቲቪ ፕሮግራሞች

የዋልታ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ዝርዝር

የፕሮግራሙ ስም የፕሮግራሙ ይዘት ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ፖስተር
ዜና • በቀን ስድስት ጊዜ የሙሉ ሰአት ዜና የሚቀርብ ሲሆን፤ ዜናዎቻችን የተለያዩ ንዑስ ዜናዎችን ይይዛሉ፡- • የሃገር ውስጥ ዜና፣ የጎረቤት ዜና፣ የአለም ዜና፣ • ሳይ-ቴክ፣ ቢዝነስ ዘገባ፣ የአየር ሁኔታ፣ የህይወት ዘዬ እና ስፖርት ናቸው፡፡ ከሰኞ እስከ እሁድ • ጠዋት ከ12፡30-1፡30፣ ከ3፡30-4፡30፣ • ቀን ከ6፡30-7፡30፣ ከ9፡30-10፡30፣ • ምሽት ከ1፡30-2፡30 እና ከ4፡00-5፡00
የእሁድ ሰበዞች • በውስጡ የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ የሆኑ ፓኬጆችን የሚያካትት የመዝናኛ ፕሮግራም ነው፡፡
የእሁድ ሰበዝ ፓኬጆች:-
የጥበብ ገበያ፡- በፊልም፣ በቲአትር፣ በሙዚቃ፣ እና በመፅሀፍ ዙሪያ አዲስ ስራ ያዘጋጁ ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚቃኝበት እንዲሁም የሳምንቱ የቦክስ ኦፊስ መረጃዎችንም የሚያካትት ባለ አስር ደቂቃ ፓኬጅ ነው፡፡

• እንገባበዝ፡- ሰሞነኛ የሙዚቃ ክሊፖችን በአሰራሮቻቸው ዙርያ በየ ስቱዲዮዎቻቸው በመገኘት ከአቀናባሪዎቻቸው ጭምር በሚያዝናና መልኩ ሂደቱን በማሳየት በስተመጨረሻም ጋባዥ አድናቂዎች እና ሙዚቀኛው አዲሱን ሙዚቃ ለተመልካች እንዲጋብዙ በማድረግ የሚጠናቀቅ ይዘት ነው፡፡

• ስነ-ውበት፡- በስነ-ውበት ዙሪያ ከአገር ውስጥም ከውጭም የተገኙ የተለያዩ የአለባበስ፣ የፀጉር አሰራር፣ የውበት አጠባበቅ፣ የሞዴሎች ፕሮፋይል፣ እና የዲዛይነሮች ውጤት የሚቃኝበት ፕሮግራም ነው፡፡

• ስፖርት ቅምሻ ፡- አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ስፖርቶች እና በስፖርት ዙርያ በተለየ ተወዳጅነት እና ዝናን ያተረፉ ግለሰቦች ጭምር ፕሮፋይሎቻቸው የሚቃኝበት ፕሮግራም ነው፡፡

• ስለ ፍቅር፡- በዓለማችን ዙርያ ስለ ፍቅር የተፈፀሙ እጅግ አስደናቂ፣ አዝናኝ እና አስተማሪ ሆኑ ታሪኮችን በቪድዮ ተደግፎ ሚቀርብበት ይዘት ነው፡፡

• ባህል፡- በአገራችን እና በመላው ዓለም ያሉ ለየት ያሉ እና ግርምትን የሚያጭሩ አስደናቂ የባህል ዓይነቶችን የሚዳስስ ነው፡፡

•ኪነ-ዋልታ፡- የሃገራችን የኪነ-ጥበብ ስራዎችን (ሙዚቃ፣ ትያትር፣ ፊልም፣ የሙዚቃ ክሊፖች፣ ስዕል፣ ስነ-ጽሁፍ…) በመቃኘት በዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎች እንዲተቹ እና ክርክር እንዲደረግባቸው ያደርጋል፣ ለኪነ-ጥበብ እድገት ያግዛሉ የሚባሉ ሃሳቦች ይንሸራሸሩበታል፤

• ዘመን እና ሙዚቃ፡- በተመረጠ ዘመን የነበሩ ሙዚቃዎችና ሙዚቀኞች የሚዘከሩበት፣ በዘመኑ የነበሩ የአለባበስ፣ ፋሽን እና ሌሎች ትዝታዎች የሚቃኙበት ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም ነው፣
• እሁድ ቀን ከ7፡30-11፡00
ነፃ ሀሳብ • በሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ምሁራን፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና አክቲቪስቶች በመጋበዝ ሰፊ ክርክር እና ውይይት የሚደረግበት ፕሮግራም ነው፡፡ ዘወትር እሮብ ምሽት 3፡00 እስከ 4፡00
የእሁድ ቁርስ • በዚህ ፕሮግራም የጠቅላላ እውቀትን ጨምሮ የተለያዩ ግንዛቤን የሚፈትሹ ትምህርታዊ፣ መዝናኛ እና ወቅታዊ ጥያቄዎችን ለተመልካቾች በማቅረብ በቀጥታ ስርጭት የሚያሳትፍ እና አሸናፊዎች ሽልማት የሚያገኙበት ተወዳጅ ፕሮግራም ነው፤ እሁድ ጠዋት ከ4፡00-5፡20
የአዲስ ጣዕም • ወጪ ቆጣቢ የምግብ ዝግጅት እና ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ግንዛቤን በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማዳረስ፤ ጤናማ የሥነ ምግብ ግንዛቤ እንዲዳብር እና ህብረተሰቡ ከአስከፊ የጤና ችግር እንዲጠበቅ ለማስቻል፤ ለህብረተሰቡ ወጪ ቆጣቢ እና ጤናማ የሥርዓተ ምግብ ግንዛቤ ለማስተማር የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው፡፡ እሁድ ጠዋት ከ3፡30-4፡00
አብነት • በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እና በበጎ አድራጎት እንዲሁም በጀግንነት ለሃገራችን ወጣቶች አርአያ የሚሆኑ፤ የኢትዮጵያውያን ታሪክ በራሳቸው በታሪከኞቹ አንደበት የሚቀርብበት እና የሚመሰገኑበት ፕሮግራም ነው፤ ቅዳሜ ቀን ከ11፡00-12፡00
አለም በዋልታ • የተለያዩ የአለማችን ሃገራት ታሪክ፣ ባህል፣ ኃይማኖት፣ መልከአምድራዊ አቀማመጥ፣ በውስጣቸው ስለያዙት ሃብት፣ ስለፖለቲካዊና መንግስታዊ አወቃቀር እና ከኢትዮጵያ ጋር ስላላቸው ቁርኝት ወዘተ አጠቃላይ ሁኔታ በሚያምር አተራረክ የሚያስተዋውቅ ፕሮግራም ነው፤ እሁድ ምሽት ከ2፡30-3፡00
ተገልጋይ • የተለያዩ ተመልካቾች ተደጋጋሚ ጥያቄ በሚያቀርቡባቸው ጉዳዮች ላይ፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ስቱዲዮ በመገኘት በቀጥታ ስርጭት መልስ የሚሰጡበት ፕሮግራም ነው፤ ቅዳሜ ቀን ከ8፡00-10፡00
መንገደኛ ጋዜጠኛ • የተቋማትን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚስቃኝ፣ የፋብሪካዎች የምርት ሂደት የሚያሳይ፣ አዳዲስ ወደ ገበያ የተቀላቀሉ ድርጅቶች የሚተዋወቁበት እና ነባር ድርጅቶች አዳዲስ ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት ፕሮግራም ነው፤ ቅዳሜ ቀን ከ10፡00-10፡30
ግማሽ ጨረቃ ተከታታይ ድራማ • የተለያቸውን ቤተሰቦቹን ለማግኘት፣ የጎዱትን ሰዎች ለመበቀል እና ፍትህን ለማስከበር ጥረት በሚያደርግ ገጸ-ባህሪ፣ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ህይወት ላይ የሚያተኩር ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው፤

• ተዋንያን፡- ሽመልስ አበራ፣ መቅደስ ጸጋዬ፣ ሄለን በድሉ፣ ታምሩ ብርሀኑ፣ ቅድስት ገ/ስላሴ፣ ሄኖክ አለማየሁና ሌሎች አንጋፋ እና ወጣት ተዋንያን ይሳተፉበታል፤

• በመቅዲ ፕሮዳክሽን የሚዘጋጅ

• ደራሲ፦ ውድነህ ክፍሌ ዳይሬክተር፦መቅደስ ጸጋዬ
ዘወትር አርብ ማታ ከ3፡00-3፡30 መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም ይጀምራል


 

የማስታወቂያና የስፖንሰር ሺፕ ዋጋዎች ዝርዝር


የድራማ የማስታወቂያ እና የሰፖንሰር ዋጋ

የድራማ ስፖንሰር አድራጊዎች የሚየገኙት ጥቅም

  1. የአንድ ክፍል ስፖንሰር የሚያስገኘው ጥቅም (Benefit Packages)
  • ሁለት ጊዜ እስከ 60 ሰከንድ ርዝማኔ ያለው ማስታወቂያ ይተላለፍለታል፤
  • የስፖንሰር አድራጊው ሎጎ በድራማው መሀል 2 ጊዜ ለ10 ሰከንድ (brought to you) እንዲታይ ይደረጋል፤
  • ድራማው ከመጀመሩ በፊት የድራማው ስፖንሰር መሆኑ በሎጎ ይገለጽለታል፤
  • የድራማው ስፖንሰር መሆኑ በስክሮል ፅሁፍ ይገለፅለታል፤
  • ከላይ የተዘረዘሩት የስፖንሰር ጥቅሞች ድራማው ሲደገም ይደገማሉ፤

  2.የሶስት ወር (አስራ ሁለት ክፍል) ስፖንሰር የሚያስገኘው ጥቅም (Benefit Packages)

  • ሁለት ጊዜ የእስከ 60 ሰከንድ ርዝማኔ ያለው ማስታወቂያ ይተላለፍለታል፤
  • የስፖንሰር አድራጊው ሎጎ በድራማው መሀል 2 ጊዜ ለ10 ሰከንድ (brought to you) እንዲታይ ይደረጋል፤
  • ድራማው ከመጀመሩ በፊት የድራማው ስፖንሰር መሆኑ በሎጎ ይገለጽለታል፤
  • የድራማው ስፖንሰር መሆኑ በስክሮል ፅሁፍ ይገለፅለታል፤
  • በአጠቃላይ ድራማው ሲደገም ጨምሮ በሶስት ወር (በአስራ ሁለት ክፍል) ውስጥ 48 ጊዜ እስከ 60 ሰከንድ ርዝማኔ ያለው ማስታወቂያ ይተላለፍለታል፤

   3.የመደበኛ ፕሮግራሞች የስፖንሰር ዋጋ


የመደበኛ ፕሮግራሞች የስፖንሰር አድራጊዎች የሚየገኙት ጥቅም

  • ሶስት ጊዜ የ30 ሰከንድ ርዝማኔ ያለው ማስታወቂያ በፕሮግራሙ ላይ ይተላለፍለታል፤
  • የስፖንሰር አድራጊው ሎጎ በፕሮግራሙ መሀል ሶስት ጊዜ ለ10 ሰከንድ እንዲታይ ይደረጋል፤
  • በስክሮል ጽሁፍ ሶስት ጊዜ የፕሮግራሙ የእለቱ ስፖንሰር መሆኑ ይገለጽለታል፤

የማስታወቂያና እና ስፖንሰር የድግግሞሽ ቅናሽ መጠን

          የማስታወቂያ የድግግሞሽ ቅናሽ መጠን

  • ከ1-15 ድግግሞሽ ———-ቅናሽ የለውም
  • ከ16-50 ድግግሞሽ———5%
  • ከ51-75 ድግግሞሽ——– 10%
  • ከ76-100 ድግግሞሽ——– 15%
  • ከ101 -150 ድግግሞሽ——– 20%
  • ከ151 በላይ ድግግሞሽ——– 30%፤

ማስታወሻ፡ ድርጅቱ በክፍያ የሚያስተላልፈውን የማስታወቂያ ድግግሞሽ ብዛት ታይቶ በኮርፖሬታችን ውሳኔ ተጨማሪ ማስታወቂያዎችን በነፃ/ቦነስ እናስተላልፋለን፡፡

          የስፖንሰር የድግግሞሽ ቅናሽ መጠን

  • ከ1-6 ድግግሞሽ—————–ቅናሽ የለውም
  • ከ7-13 ድግግሞሽ——————-5%
  • ከ14-26 ድግግሞሽ——————–10%
  • ከ27-40 ድግግሞሽ———————–15%
  • ከ41 በላይ ድግግሞሽ————————-20%