ለሱዳናዊያን መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ከሱዳን ወንድም እና እህቶቹ ጎን እንደሚቆም አረጋገጡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሱዳን የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በአረብኛ ቋንቋ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታታለ መሆኑን ገልጸዋል::
‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብም ለሱዳን መረጋጋት እና ሰላም ከሱዳን ውንድም እና እህቶቻን ጎን እንቆማለን›› ብለዋል፡፡
ሱዳን ውደ ቀደመ ሰላሟ በቅርቡ እንደምትመለስም እምነቴ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልእክታቸው አስፍረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በአገራት የውስጥ ጉዳዮች የሚደረጉ የውጭ ጣልቃ ገብነትን አውግዘዋል፡፡