ለሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የማዕረግ እድገት ተሰጠ

ጥቅምት 11/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ በተለያዩ ቦታዎች ለግዳጅ ተሰማርተው ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት የማዕረግ እድገትና ሽልማት ሰጡ።

በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራ ከፍተኛ የክልሉ ልዑክ ወደ ተለያዩ ግዳጆች ተሰማርተው በድል የተመለሰውን የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላትን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት የማዕረግ ዕድገትና ሽልማት ተሰጥቷል።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ም/ኮ መሀመድ አህመድ በስነሥርዓቱ ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል በተለያዩ ቦታዎች ሀገር ለማዳንና ሰላምን ለማስከበር የፈፀማቸውን ጀግንነት ህዝባቹ ኮርቶባቿዋል፤ ወታደር ትናንት ከግዳጅ ሲመጣ፣ ነገም ለግዳጅ መዘጋጀት የወታደር ስራ ነው ብለዋል።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሙበሽር ዱበድ በበኩላቸው፣ እንደ ቢሮ የክልሉን ልዩ ኃይልና የፀጥታ ተቋማት ለማጠናከር በሰፊው ተሰርቷል አሁንም የበለጠ ይሰራል ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ከለውጡ ማግስት ልዩ ኃይሉ ይበተናል የሚል አሉባልታ ፀረ ለውጥ በሆኑ ሰዎች ሲናፈስ ነበር፤ ነገር ግን ባለፉት ሦስት ዓመታት እናንተ በሰራችሁት ስራ ህዝባቹና ሀገራቹ ኮርቶባቹዋል ብለዋል።

አሁን ላይ እንደ ሀገር እና እንደ ክልል ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግረናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ይህን አዲስ ምዕራፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ አካላት በመኖራቸው ህግን ለማስከበር በሚደረገው ስራ የእናንተ ሚና ከፍተኛ ነው ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!