ለኤች አር 6600 አርቃቂዎች የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን አባላት የገንዘብ ክፍያ መፈጸማቸው ተጠቆመ

መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) ለኤች አር 6600 አርቃቂዎች በተለያዩ አገራት የሚገኙ የሽብርተኛው ሕወሓት ቡድን አባላት የገንዘብ ክፍያ መፈጸማቸው የተጠቆመ ሲሆን ይህም የቡድኑ አባላት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርጉት ጥረት እንደቀጠለ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ሚራክል ናይን የተባለ የመዋቢያ ዕቃዎች አምራች ኩባንያ ባለቤትና የሽብር ቡድኑ ደጋፊ ሊሊ ገሰሰ ለኮንግረስ አባላት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓ ከታማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ ተረጋግጧል፡፡

ይህች ሴት ለረቂቅ ህጉ ጠንሳሽ ለኒውጀርሲው ሴናተር ቶም ማሊኖውስኪ 2 ሺሕ ዶላር፣ ለካሊፎርኒያዊ ብራድ ሼርማን 6 ሺሕ ዶላር እና ለኒው ዮርኩ ግሪጎሪ ሚክስ 2 ሺሕ 900 ዶላር መክፈሏን የመረጃው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!