መብትን በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ያመጣው ፍሬ

ጥቅምት 11/2014 (ዋልታ) በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ነዋሪዎች መብታችንን በሰላማዊ መንገድ ጠይቀን ያገኘነው ምላሽ እጅግ አስደሳች ነው ሲሉ ገለጹ።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለዋልታ በሰጡት አስተያየት ለዘመናት ክልል የመሆን መብታችንን በሰላማዊ መንገድ ስንጠይቅ ኖረን በትዕግስት በመጠበቃችን ዛሬ ላይ ድምጻችን ተሰምቶ ለጥያቄያችን ተገቢውን ምላሽ በማግኘታችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።
ከዚህ በፊት ታቅፈውበት የነበረው የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ህዝቦች ክልል ማዕቀፉ ሰፊ ስለሆነ በርካታ እንግልት እና የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረበት በመሆኑ ማህበረሰቡ ፍትህን ለማግኘት ከሚጓዘው ረጅም እርቀት የተነሳ ሀብት እና ንብረቱን ጨርሶ መፍትሄ ሳያገኝ ተስፋ ይቆርጥ እንደነበረ ነው የተናገሩት።
አሁን ግን የክልልነት ጥያቄው ውሳኔ ማግኘቱ ህብረተሰቡ ያወጣ የነበረውን ጉልበት እና ገንዘብ ለከተማው እድገት በማዋል ዘርፈ ብዙ ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል ነው የገለጹት።
የለውጡ መንግስት ካለፈው ጊዜ የተሻለ ጥያቄን የሚሰማ እና የሚመልስ በመሆኑ በኃይል ሳይሆን በሰላም መፍትሄ ማምጣት ችለናል ታግሰን በመጠበቃችን ፍሬውን ማየት ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።
በሔለን ታደሰ (ከሚዛን አማን)
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!