ም/ርእሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን የከሬብ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ጎበኙ

                                                 አቶ ርስቱ ይርዳው

የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የከሬብ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደትን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ2008 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ በዲዛይን ለውጥ እና በበጀት እጥረት ምክንያት የግንባታ ስራው መጠናቀቅ አለመቻሉ ተገልጿል ።

ፕሮጀክቱ በደቡብ ክልል መንግስት እንደሚገነባና 299 ሚሊየን ብር እንደተበጀተለት ተነግሯል።

በተጨማሪ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የግንባታ አፈፃፀም 70 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 2ሺህ 5 መቶ አባወራዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጉብኝቱ ወቅት የተገለጸ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ ለማህበረሰቡ ክፍት እንደሚሆንም ተጠቁሟል።

(በዙፋን አምባቸው)