ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ የክልሉን ልዩ ኃይል አባላት አመሰገኑ

ጥር 30/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እያደረጉ ያሉትን ተሳተፎ አመሰገኑ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸውን ባሰፈሩት ጹሑፍ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰላምና ፀጥታን ከማስጠበቅ ጎንለጎን በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳትና ለመታደግ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ልዩ ኃይሉ እየሰራው ያለው ሥራ በአርአያነት የሚወሰድ ተግባር በመሆኑ እናደንቃለንም ሲሉ ነው ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፋ ይጻፉት።
በሶማሌ ክልል 9 ዞኖች በተከሰተው የድርቅ አደጋ 960 ሺሕ በላይ ዜጎች ቀጥተኛ ተጎጂ በመሆናቸው የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ የፌደራሉ መንግሥት ጥር 25 በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።
በአጠቃላይ በክልሉ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች የእለት ደራሽ ድጋፍ ይፈልጋሉ ያለው መንግሥት እስከ ታኅሣሥ ድረስ 558 ሺሕ ኩንታል እህል በማሰራጨት 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎችን ማዳረስ እንደተቻለ ጠቁሟል፡፡
የክልሉ መንግሥት ከ15 ቀን በፊት በሰጠው መግለጫ በድርቁ ከ250 ሺሕ በላይ እንስሳት እንደመቱ ማሳወቁ ይታወሳል።