ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በዱግዳና ቦራ ወረዳዎች በክላስተር እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው

ነሐሴ 1/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳና ቦራ ወረዳዎች በክላስተር እየለማ ያለውን የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ የስንዴ ክላስተር ጉብኝታቸውን ቦራ ወረዳ ባርታ ሳሚ ቀበሌ የጀመሩ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ ዞን ከ280 ሺሕ ሄክታር በላይ በተለያዩ ሰብሎች በኩታ ገጠም እየለማ ይገኛል።

ከዚህ ውስጥ 188 ሺሕ ሄክታር በስንዴ ብቻ በክላስተር እየለማ መሆኑ መገለጹን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

በኦሮሚያ ክልል ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም በስንዴ ዘር መሸፈኑም ተገልጿል።