ሽብርተኛውን ትሕነግ የመደምሰስ ሥራ

ነሐሴ 26 /2013 (ዋልታ) – አገር የማፍረስ እኩይ ዓላማን አንግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ትሕነግ የሽብር ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን እየተደመሰሰ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ሰይፉ ሰይድ እንዳሉት ዞኑ ከአጎራባች ዞኖች ጋር የጠበቀ አደረጃጀት በመፍጠር ወራሪውን እና ሽብርተኛውን ትሕነግ የመደምሰስ ሥራ እየተሠራ ነው።
ከመደበኛ ጸጥታ ኃይሉ በተጨማሪ ወጣቶች ተደራጅተው ግንባር ድረስ በመዝመት አገርን ለመታደግ ከሽብርተኛው ቡድን ጋር እየተፋለሙ ነው ብለዋል።
የሽብርተኞቹን ኦነግ ሸኔና ትሕነግ ሴራ ለማክሸፍ ከአጎራባች ዞኖች ጋር እየሰሩ መሆናቸውንም ነው ምክትል አስተዳዳሪው ለአሚኮ የገለፁት፡፡
ቡድኑን ከማፅዳት ጎን ለጎን ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም ለኅልውና ዘመቻው ሁሉን ዐቀፍ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደቀጠለም በመጥቀስ፤ ከሕዝቡ 95 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን አሳውቀዋል፡፡