በሀረሪ ክልል ህወሐትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – በሀረሪ ክልል አሸባሪው ህወሐትና ሸኔን የሚያወግዝ እና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

የአሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ ያልተቀደሰ ጋብቻ ሀገርን ለመበታተን ያሴሩት ሴራ እንጂ የማንንም ብሔር ጥቅም ለማስከበር እንዳይደለ ከኛ ውጪ ምስክር አያስፈልግም ሲሉ ሰልፈኞቹ መናገራቸውን ከሀረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በድጋፍ ሰልፍ ላይ የሀረሪ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስራ አብደላ፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አብዱጀባር መሀመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አዲስ አለም በዛብህ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።