በሀዋሳ ከተማ የሕወሓትና ሸኔ የሽብር ድርጊቶች የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

በሀዋሳ ከተማ ሕወሓትና ሸኔ የሚያወግዝ ሰልፍ

ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ) በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሀገር አፍራሾቹን የሕወሓትና ሸኔ የሽብር ድርጊቶች የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ከሲዳማ ክልል ሁሉም ወረዳዎች እና ሀዋሳ ከተማ 8ቱ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ በማካሄድ ላይ  ናቸው።

“ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደጀን እንሆናለን! በመንጋው ላይ የጋራ ብትራችንን እናሳርፋለን!” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ያነገቡት ነዋሪዎቹ የድርጅቶቹን ሴራ ማውገዛቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።