በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሊወጣ የነበረ 2 ሺሕ 820 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ

ጥር 6/2014 (ዋልታ) ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በ141 ጀሪካን በአውቶቡስ ተጭኖ ሊወጣ የነበረ 2 ሺሕ 820 ሊትር ነዳጅ በክልሉ ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የንግድ ክትትል ባለሙያዎች መያዙ ተገልጿል።

በሌሎች የክልሉ ከተሞችን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እየታየ በጅግጅጋ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ነዳጁን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ ከተሞች እንደሚልኩ መረጃ መገኘታቸው ተጠቁሟል።

በሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርትና ኅብረት ስራ ማኅበራት ዳይሬክተር መሀሙድ አሊ በክልሉ የሚካሄደውን ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ ለማስቆም ኅብረተሰቡ ከመንግሥትና ክትትል ባለሙያዎች ጎን እንደቆሙና ድጋፍ እንደሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው ያገኘነው።