በመዲናዋ የመሬት ልማት ማኔጅመንት የስራ ኃላፊ ግማሽ ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል ተያዘ

ጥር 6/2014 (ዋልታ) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የመሬት አገልግሎት አስፈጽማለሁ በማለት ከባለጉዳይ 500 ሺሕ ብር ጉቦ ተቀብሏል የተባለ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ኃላፊ ብርሐን ጌራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።
የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ደመና ተስፋዬ እንደገለፁት ግለሰቡ የይዞታ ጉዳይ አስፈጽማለሁ በማለት ከተገልጋይ የ500 ሺሕ ብር ቼክ ሲቀበል ከአንድ ግብረ አበሩ ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው።
ተጠርጣሪው በወረዳው ሀሮን ሆቴል አካባቢ 500 ሺሕ ብር መጠን ከተፈረመነት የንብ ባንክ ቼክ ቁጥር 566322 ኤግዚቪትነት ጋር መያዙ ተገልጿል።
በ2013 ዓ.ም የተደረገውን የመሬት ማጥራትና የኦዲት ስራ ሽፋን በማድረግ የመከነ ካርታ አስተካክላለሁ በሚል ተጠርጣሪው ጉቦ መቀበሉንና እጅ ከፍንጅ መያዙን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለፈጣን መረጃዎች፦