በመዲናዋ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) -የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማዕከል ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ24 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ በአዲስ አበባ ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለማዕከሉ ግንባታ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ማዕከሉ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የሚገነባ ነው ተብሏል፡፡

ዶክተር ሳሙኤል ግንባታው የስልጠና ተደራሽነትን ማስፋት፣ የትምህርትና ሥልጠና ጥራትን ማሻሻል እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርን ማጠናከርን ዋና ዓለማው ያደረገ ነው ብለዋል።

ማዕከሉ በብረታ ብረት እንዲሁም ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

በስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ወርክሾፖች ጉብኝትና የችግኝ ተከላ መከናወኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።