በሴካፋ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ አሸኛኘት ተደረገለት

ነሐሴ 1/2014 (ዋልታ) ታንዛኒያ በምታዘጋጀው የሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ አሸኛኘት ተደረገለት።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ያሸነፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ በታንዛኒያ በሚካሄደው የምስራቅ እና መካከለኛ አፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደር ይሆናል።
ክለቡ አምናም ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ ላይ ተሳትፎ ውድድሩን በሁለተኛነት ያጠናቀቀ ሲሆን ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳተፍ ይሆናል።
በሽኝት ሥነ ሥርአቱ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ የእግር ኳስ ክለቡ በውድድሩ ላይ የተሳካ ጊዜ እንዲያሳልፍ በመመኘት ለስኬት እንዲበቃም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በሥነ ሥርአቱ ላይ የክለቡ አሠልጣኝ እና አምበል ከባንኩ ፕሬዝዳንት የባንዲራ ርክክብ በማድረግ በድል ለመመለስ ቃል ገብተዋል።
በታንዛኒያ በሚካሄደው ውድድር ያሸነፈው ክለብ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው አህጉር አቀፍ የክለቦች ውድድር ላይ የሚሳተፍ ይሆናል።
በትዝታ ወንድሙ