በቱርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡትን 27 ሺሕ ዶላር አስረከቡ

ጥር 7/2014 (ዋልታ) በቱርክ የሚኖሩና የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተቀብለው የመጡ የኢትዮጵያዊያን አንድነትና ትብብር ማኅበር አባላት ለተፈናቀሉ ወገኖች ያሰባሰቡትን 27 ሺሕ ዶላር አስረከቡ።

የማኅበሩ የቦርድ አባላት ድጋፉን በቱርክ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆኑ ቱርካውያን ማሰባሰባቸውን ከዳያስፖራ ኤጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ድጋፉን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ (ዶ/ር) በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከማይኖሩበት አገር የተሰባሰበው ድጋፍ የማኅበሩ አባላት ያደረጉትን ጥረት የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።