በትግራይ ከ4 ሺህ ኩንታል በላይ የእርዳታ ስንዴ ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች ተያዙ

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – በትግራይ ለተፈናቀሉ ወገኖች በእርዳታ የቀረበ 4ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ አየር በአየር ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰው ለኢዜአ እንደገለፁት ለተፋናቃዮች የመጣ የእርዳታ እህል ሰሞኑን አየር በአየር ለመሽጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ስምንት ሰዎች ተይዘዋል።

ግለሰቦቹን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጠርጣሪ ግለሰቦቹ እጅ የነበረ የእርዳታ ስንዴን ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲከፋፈል መደረጉን አመልክተዋል።

“ለተፈናቃይ ወገኖች የቀረበ  የእርዳታ  ስንዴ ዘርፎ ለግል ጥቅም ለማወዋል መሞከር  አፀያፊ ነው” ያሉት ሀላፊው፤  በእርዳታ የሚቀርብ እህል በአግባቡ ለተፈናቀሉ እንዲደርስ ሁሉም በንቃት ሊከታተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።