በትግራይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ተጀመረ

ኅዳር 27/2015 (ዋልታ) በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ ስራ አመራር በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት አስቸኳይ ጥገና በማድረግ በአጭር ቀናት ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም መሠረት የተለያዩ የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን መዋቀሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመለክታል፡፡

ከነገ ጀምሮ ለጥገና ስራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት ቡድኑ ወደ ክልሉ የሚሠማሩ ሲሆን በአጭር ጊዜ የጥገና ስራውን በማጠናቀቅ ህብረተሠቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናል ተብሏል፡፡