በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ዙሪያ ከተለያዩ ዓለም ዐቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውይይት ተካሄደ

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ እና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከተለያዩ ዓለም ዐቀፍ የፋይናንስ ተቋማትና አጋሮች ጋር በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “በውይይቱ የማዕድን አቅማችንን በተመለከተ ገለጻ አድርገናል” ብለዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማቱ እየተካሄዱ ያሉ የማዕድን ፕሮጀክቶችን ለማገዝ እንዲሁም የማዕድን የግል ክፍለ ኢኮኖሚን በፋይናንስ ለመደገፍ ፍላጎታቸውን መግለጻቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW