በኢንጅነር ስመኘው በቀለ እና በአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ስም ጎዳና ተሰየመ

ጎንደር፣ ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) – በጎንደር ከተማ በቀደሞው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ እና በአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ስም ጎዳና ተሰየመ፡፡
ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በር እስከ ኮሌጅ ማዞሪያ ያለው የአስፓልት መንገድ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ ) ጎዳና በመባል ተሰይሟል፡፡
ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በር እስከ ሽንታ ወንዝ ድልድይ ያለዉ የአስፓልት መንገድ ደግሞ በኢ/ር ስመኘው በቀለ ስም ነው የተሰየመው።
(በሳሙኤል ሀጎስ)