በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት የሚገልጽ ዝግጅት አካሄዱ

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጽ ዝግጅት አካሂደዋል።

የመከላከያ ሰራዊት በከሃዲውና ጽንፈኛው ህወሓት ቡድን የተቃጣበትን ጥቃት መክቶ በፍጥነት ኢትዮጵያን ወደ ድል ብስራት በማሸጋገሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ለመከላከያ ሃይል ድጋፍ ለማድረግና በጽንፈኛው ህወሓት ርጥባን ተከፋዮች የሚነዛውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ለማክሸፍ እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።

ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ መሆኑን በዋሽንግተን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።