በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

ጥር 30/2014 (ዋልታ) በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራና የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሚና መሀመድን ያካተተ ከፍተኛ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ።

ለልዑኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

ልዑኩ በቆይታው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡