ባለስልጣኑ ባለፉት 9 ወራት ከ155 ሺሕ በላይ ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 9 ወራት ከ155 ሺሕ በላይ ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በህገ-ወጥ ማስታወቂያ መከላከል ዙርያ እየመከረ ነው።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አባይነህ ገዳሙ የውይይቱ ዓላማ በህገ-ወጥ ማስታወቂያ ዙርያ የቅድመ መከላከል ተግባራትን ከባለድርሻ ጋር በጋራ በማከናወን ደንብ መተላለፍ መቀነስ መሆኑን ገልጸዋል።

የዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ፈቃድ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ስጦታው አካለ በበኩላቸው ውይይቱ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ባለድርሻ አካላት የህገ-ወጥ ማስታወቂያ ላይ በጋራ በመከላከል፣ በመቆጣጠር እና እርምጃ በመውሰድ የከተማዋን ገፅታ ፅዱ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በውይይቱ የግል ማስታወቂያ ድርጅቶችና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በአሳንቲ ሀሰን

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW