አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶዝ በላይ የፋይዘር ክትባት ድጋፍ አደረገች

ጥር 20/2014 (ዋልታ) አሜሪካ ለኢትዮጵያ 1 ሚሊየን 680 ሺሕ 120 ዶዝ ፋይዘር የኮሮና ቫይረስ ክትባት ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉ በተያዘው ሳምንት በኮቫክስ ጥምረት አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ መግባቱን በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

የተደረገው ድጋፍ አሜሪካ የኮሮና ቫይረስን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑም ተገልጿል።