አትሌት መዲና ኢሳ የቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር አሸነፈች

የቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ

መጋቢት 17/2015 (ዋልታ) የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር በአትሌት መዲና ኢሳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በዚህ ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ በመሪነት ያጠናቀቀች ሲሆን ፅጌ ገብረሰላማ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ እንዲሁም መልክናት ውዱ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።

ውድድሩን በአንደኝነት ላጠናቀቀችው አትሌት 70 ሺሕ ብር፣ ሁለተኛ ደረጃ ለወጣችው 45 ሺሕ ብር እንዲሁም ለሦስተኛ ደረጃ 30  ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱም ተመላክቷል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው ይህ የ5 ኪ.ሜ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ ነው የተካሄደው፡፡