ከደሴ እስከ ወልዲያ ያሉት ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

ጥር 7/2014 (ዋልታ) ከደሴ እስከ ወልዲያ ሲከናወን የቆየው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመሮች የመጠገን ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

በዚህም በሁለቱ ትልልቅ ከተሞች መካከል የሚገኙት አካባቢዎች ኃይል ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

ጥገናው ትናንት ምሽት ቢጠናቀቅም መስመሩ በሚያልፍበት አካባቢ በደሴ እና በሐይቅ መካከል እንዲሁም መርሳ አካባቢ የበቀለ ዛፍ ከመስመሩ ጋር ተገናኝቶ ባለመቆረጡ የተነሳ ኤሌክትሪክ ማገናኘት አልተቻለም ነበር ብሏል።

ይሁንና ዛሬ ዛፎቹ በመቆረጣቸውና ኃይል ለመስጠት የሚያግድ ነገር ባለመኖሩ ከተሞቹ ኤሌክትሪክ ማግኘት መቻላቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡