ክልሉ ከመንግሥት የልማት ተቋማት አመራሮች ጋር እየመከረ ነው

ሰኔ 7/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከመንግሥት የልማት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር የእቅድ ውይይት እያደረገ ነው።

መድረኩንም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አሰጀምረውታል።

ውይይቱ መንግሥት በልማት ዙርያ ያለውን ፍላጎትና ቅድሚያ ሚሰጣቸው ጉዳዮችን በተመለከተ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ያወጣቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እቅድ ለማሳካት የልማት ድርጅቶች በትጋት መስራት እንዳለባቸው ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።

በውይይቱ የቀጣይ አቅጣጫና መመሪያዎች ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡