የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ

ነሐሴ 1/2014 (ዋልታ) የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥም ነው ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡