“የብሔራዊ ውይይቱ አንኳር ጉዳዮች እና አገራዊ ፋይዳው” በሚል የጉሚ በለል ውይይት እየተካሄደ ነው

18ኛው የጉሚ በለል የውይይት

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) 18ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ “የብሔራዊ ውይይቱ አንኳር ጉዳዮች እና አገራዊ ፋይዳው” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የብሔራዊ መግባባት የውይይት መድረክ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ ንግግር ያደረኩት የፖለቲካ ምሁሩ ሌንጮ ለታ አሁን ላለችው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚያስፈልገው መልቲ ናሽናልዝም መሆኑን ገልጸው ለአገሪቱ የክርክር መድረክ ሳይሆን የውይይት መድረክ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የውይይት መድረክ የሚያስፈልገው ሰለም ስለሌለ ሳይሆን ያለውን ሰላም፣ መግባባት፣ አንድነት እና ዴሞክራሲን ለማጠናከር መሆኑንም አክዋል፡፡

የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም ልዩነትን ወደ አንድ በማምጣት አብሮ መጓዝ የምቻልበትን መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ እንደሆነም አመላክተዋል።

በአሳንቲ ሀሰን