የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

መጋቢት 17/2015 (ዋልታ) የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሌሎች እምነት ተቋማት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ነው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተፈጸመው።

የሁለቱ ብፁዓን አባቶች የሽኝት መርኃ ግብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካሄዱን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ አመላክቷል።