የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት መግለጫ

ጥቅምት 11/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በዛሪማ ከተማ በሚገኘው መስጂድ ላይ የፈፀመውን ውድመት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አወገዘ።
የሽብር ቡድኑ በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ ዛሪማ ከተማ በሚገኘው መስጂድ ላይ ጥቅምት 7 በከባድ መሳሪያ ያደረሰውን ውድመት እንደሚያወግዝ ነው ምክር ቤቱ ለአሚኮ በላከው መግለጫ ያስታወቀው፡፡
በአሁኑ ወቅት አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል በአማራ ክልል ላይ እየፈጸመ በሚገኘው ጦርነት በሕዝቦች ሕይወት ላይ አስከፊ ግድያ እና መፈናቀል በየቀኑ የሚሰማ መርዶ ሆኖ ቀጥሏል ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ በዜጎች፣ በሕዝብ መገልገያ ተቋማትና መሠረተ ልማቶች ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት አሳዛኝ ነው ብሏል።
በሰሜን ወሎ፣ በዋግ ኽምራና በደቡብ ወሎ አካባቢዎችም በርካታ መስጂዶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አማኞችም ተጎድተዋል ያለው መግለጫው ዝርዝሩ ወደፊት በጥናት የሚገለፅ መሆኑንም አመላክቷል።