የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል

የካቲት 24/2013 ዓም (ዋልታ ) – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ በምክር ቤቱ የፕሬስና ህዝብ ግነኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ አለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2013 ዓ.ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ይገመግማል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ አቶ አዲስ አለም ተናግረዋል፡፡

(ምንጭ:- የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት)