የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‘የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ’ ሽልማትን አሸነፈ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2022 ‘የአፍሪካ ተወዳጁ አየር መንገድ’ ሽልማት ማሸነፉን አስታወቀ፡፡

ግሎባል ትራቭል ማጋዚን ‘ትሬዚስ አዋርድ’ በተሰኘው ውድድር ድምጽ የማሰባሰብ ሂደት አየር መንገዱ አሸናፊ የሚያደርገውን ድምጽ ማግኘቱን አመላክቷል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያሸነፈው በተከታታይ ለ3ኛ ጊዜ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጅ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም በደንበኞቻችን ዘንድ የአፍሪካ ተመራጩ አየር መንገድ እንድንሆን ድምጻቸውን ስለሰጡን እናመሰግናለን፤ ኩራትም ይሰማናል ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW